Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የወዳጇን ውለታ አትዘነጋም- ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የወዳጇን የሜክሲኮ ዉለታ እንደማትዘነጋ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ገለጹ ፡፡
ኢትዮጵያ በውስጥና በውጭ በተለይም በጣሊያን ወራሪዎች ተወርራ በነበረበት ወቅት ሜክሲኮ ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፋ አኩሪ ታሪክ እንዳስመዘገበች ሰብሳቢው አውስተዋል፡፡
የሜክሲኮ ዜጎች ለኢትዮጵያ ለከፈሉት አኩሪ መስዋዕትነት ኢትዮጵያ በሜክሲኮ ስም በአዲስ አበባ ከተማ አደባባይ እንደገነባችና የተከፈለላትን ውለታም እንደማትዘነጋ ዶክተር ነገሪ ተናግረዋል፡፡
ሰብሳቢው ይህን የገለጹት በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር ቪክቶር ማኑኤል ትረቪኖን ጋር በዛሬው እለት በተወያዩበት ወቅት ነው።
71 አመታትን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊው ዴፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ በንግድ፣ በቱሪዝም ፣ በትምህርት፣ በስራ ዕደል ፈጠራ ፣ በኢንቨስትመንትና በግብርናው ዘርፍ ከሜክስኮ ጋር በጋራ እንደምትሰራ ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ነገሪ አያይዘውም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚከናወኑ ስራዎችን አስመልክተው ለአምባሳደሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም ግድቡ የሚገነባበት ዋና ዓላማ ለመስኖ ፕሮጀክት ሳይሆን የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጨት ከ 60 በመቶ በላይ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጨለማ ለማውጣት እንደሆነ አስረድተዋል ፡፡
ኢትዮጵያ የትኛውንም ሀገር የሚጎዳ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንደማትከተል ጠቅሰው ÷ የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት በተለይም ግብጽ ከዚህ ተቃራኒ በመሆንና የጋራ ተጠቃሚነት መርህን በመጣስ ላይ መሆኗን ለአምባሳደሩ አብራርተውላቸዋል ፡፡
ከዚያም ባለፈ ዶክተር ነገሪ በትግራይ ክልል የተከናወነውን የሕግ ማስከበር እርምጃ አስመልክተው ለአምባሳደሩ አብራርተውላቸዋል፡፡
በአምባገነኑ የሕወሓት ቡድን ላይ የተወሰደው እርምጃ እንደተጠናቀቀና በክልሉ ሰላም መስፈን እንደቻለ አስረድተው ÷ በሕግ ማስከበር እርምጃው ከቀያቸው ተፈናቅለው ለነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች መንግስት አስፈላጊውን የሰብዓዊ እርዳታ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
መንግስት ሕገ-ወጥ ቡድኑ ያፈራረሳቸውን መሰረተ-ልማቶች ወደነበሩበት የመመለስ ስራ እየሰራ መሆኑን ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ምርጥ የቱሪስት መዳረሻ ከሆኑ አሥር የአለማችን ሀገሮች አንዷ መሆኗን ሰብሳቢው ጠቅሰው ፣ የቱሪዝም ዘርፉን የበለጠ ለማስፋት ከሜክሲኮ ጋር በጋራ እንደሚሰራ አብራርተዋል ፡፡
ከኢትዮጵያ ሕዝብ 70 በመቶው ወጣት እና ቁጥሩ በርካታ የሆነ የተማረ የሰው ሃይል መኖሩን ገልጸው÷የሜክሲኮ ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በምጣኔ ሀብት፣ በኢንቨስትመንት ፣ በቱሪዝምና በንግዱ ዘርፍ እንዲሰማሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አምባሳደር ትረቪኖ በበኩላቸው÷ ምርጥ አየር መንገድ አላችሁ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻውን ሜክሲኮ ያደረገ በአፍሪካ ብቸኛው አየር መንገድ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በአለም የኢትዮጵያ አምባሳደር በሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ሀገራቸው በምጣኔ ሀብት፣ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ በንግድና በግብርና ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራ አምባሳደር ትረቪኖ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደሩ አክለውም የሀገራቸው ባለሃቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ለማድረግ እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.