Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ እና ቻይና የገቡትን የንግድ ፍጥጫ ያረግባል ያሉትን የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ቻይና አዲስ የንግድ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታወቁ።

ሃገራቱ በዋሽንግተን የገቡትን የንግድ ጦርነት ያረግባል ያሉትን የንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሰረት ቻይና ከአሜሪካ የምታስገባቸውን ሸቀጦች መጠን ለመጨመር ተስማምታለች።

በዚህም ቤጂንግ ከአሜሪካ የምታስገባውን ሸቀጥ ቢያንስ በ200 ቢሊየን ዶላር ለማሳደግ ስምምነት ደርሳለች።

ከዚህ ባለፈም ቻይና ተመሳስለው የሚሰሩና ገበያ ላይ የሚውሉ ምርቶችን በመቆጣጠር ረገድ ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግ እና የንግድ ስርቆትን ለመከላከል መስማማቷም ነው የተነገረው።

በአንጻሩ አሜሪካ ከቻይና በምታስገባቸውና 360 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ባላቸው ምርቶች ላይ የምትጥለውን እስከ 25 በመቶ የሚደርስ ቀረጥ የምታስቀጥል ይሆናል።

ከዚህ ባለፈ ግን በቅርቡ ወደ አሜሪካ በሚገቡ የቻይና ምርቶች ላይ የተጣለውን ተጨማሪ ቀረጥ ታነሳለች።

የሁለቱን ሃገራት ስምምነት ተከትሎ ዓለም አቀፉ የአክሲዮን ገበያ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈም እንደ ነዳጅ ባሉ ምርቶች ላይ የዋጋ መነቃቃት ታይቷልም ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.