Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ውስጥ በተከሰተው ቫይረስ አራት ስዎች መሞታቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ውስጥ በተከሰተው ቫይረስ እስካሁን አራት ስዎች መሞታቸው ተገለፀ፡፡

ይህ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃው ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው በቻይና ውሃን ግዛት ውስጥ ነው፡፡

በዚህም እስካሁን አራት ሰዎች መሞታቸው  የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ቤጂንግ እና ሻንጋይን ጨምሮ በቻይና ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ ከ200 የሚበልጡ ከበሽታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሪፖርት ተደርገዋል ፡

የቻይና ብሔራዊ የጤና ኮሚሽን እንዳስታወቀው በቻይና ጓንግዶንግ አውራጃ ውስጥ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ይህም ከሰው ወደ ሰው የተላለፈ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይም በዊሃን ግዛት ቢያንስ 15 የህክምና ሰራተኞች በቫይረሱ መጠቃታቸው እና ከእነዚህም አንዱ በከባድ ሁኔታ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

በቫይሩሰ የተጠቁት ግለሰቦቹ ህክምና እየተደረገላቸው ለብቻቸው  እንዲቆዩ  ተደርጓል ብለዋል፡፡

ሌሎች ይህን ይበሉ እንጂ የእንግሊዝ የሕክምና ባለሙያዎች ግን 1 ሺህ 700 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል እያሉ ነው።

ይህን ተከትሎም ሲንጋፖር እና ሆንግ ኮንግ ከቻይና ውሃን ግዛት የሚመጡ ተጓዦችን መርምረው ማስገባት ጀምረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስም ብትሆን በሳን ፍራንሲስኮ፣ ሎስ አንጀለስ እና ኒው ዮርክ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች በኩል የሚያልፉ መንገደኞች እንዲመረመሩ ትዕዛዝ አሳልፋለች።

ከዉሃን ወደ ሲድኒ የሚመጡ መንገደኞችን መመርመር  እንደሚጀምሩም የአውስትራሊያው ባለስልጣናትም አስታውቀዋል ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.