Fana: At a Speed of Life!

በካናዳ ሰስካቹዋን ግዛት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ22 ሺህ በላይ የካናዳ ዶላር ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በካናዳ ሰስካቹዋን ግዛት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ22ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ ተሰብስቧል፡፡

በካናዳ የሚገኘው የጥምረት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የሰስካቹዋን ግዛት ቻፕተር በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ነው የቨርቹዋል ኮንፈረንስ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የተዘጋጀው፡፡

በዚህም ከ12ሺህ ዶላር በላይ ነጻ ድጋፍ የተደረገ እና ቃል የተገባ ሲሆን፥ ከ10ሺህ ዶላር በላይ የቦንድ ግዢ በቀጥታ ከአገር ቤት ለመፈጸም ቃል ተገብቷል።

በገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት በካናዳ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፥ በአጠቃላይ በካናዳ የሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን ለህዳሴ ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

በተጨማሪም የግድቡ ግንባታ ከዳር እንዲደርስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካለችበት ውስብስብ ሁኔታ አንፃር ሁሉም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን በአገሩ ጉዳይ አርበኛ በመሆን የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ በካናዳ የጥምረት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃላፊ ዶክተር ፍሰሃ ሰለሞን፥ በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነት እንዳላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.