Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በትግራይ ክልል ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የ181 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት በትግራይ ክልል ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚውል የ181 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ፡፡

ድጋፉ በክልሉ አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 3 ሚሊየን ዜጎች እንደሚውልም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የምግብ፣ የንጹህ መጠጥ፣ መጠለያ፣ የጤና አገልግሎትን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግቶችን ለማቅረብ እንደሚያስችልም የየአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ሃላፊ ሳማንታ ፓወር ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለአርሶ አደሮች ዘርና ማዳበሪያን ጨምሮ የግብርና ግብአትን ለማቅረብ ይውላልም ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም ድጋፉ ለማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ጫና ማገገሚያ ፕሮግራም እንደሚውልም የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.