Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ለሰላምና ልማት ከፍተኛ አስተዋፆ  ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች  እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)  በጋምቤላ ክልል ለሰላምና ልማት ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከቱ 202 ተቋማትና ግለሰቦች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ÷ በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት የተገኘውን ዘላቂ ሰላምና ልማት ይበልጥ ለማጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካል ተሳተፎውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በፊት የነበረው ከፋፋይና አግላይ የፖለቲካ አስተሳሰብ በመደመር የለውጥ ምዕራፍ ከተተካ ማግስት ጀምሮ በክልሉ በርካታ የሰላምና የልማት ድሎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

የህዝቦችን አንድነትና ወንድማማችነት በመሸርሸር ሀገር ለመበተን አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሃይሎች የግጭት ሴራቸው በጋምቤላ ክልል እንዳልተሳካላቸው ገልጸዋል።

ክልሉ ሰላም እንዲሆን የክልሉ ህዝብና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ከመንግስት ጎን የመቆማቸው ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።

የክልሉን ሰላምና ልማት ዘላቂነት ለማረጋገጥ የህዝቡና የባለድርሻ አካላት ትብብትና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።

በዕለቱ የክልሉ መንግስት ያዘጋጀው እውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር የተቋማቱንና የግለሰቦቹን የሰላምና የልማት አርአያነት ለመግለጽ በማሰብ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

እውቅና ከተሰጣቸው ተቋማት አመራሮች መካከል የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ሮን ጎኝ በሰጡት አስተያየት “ሽልማቱ የሆስፒታሉ ሰራተኞች የጋራ ጥረት ውጤት ነው” ብለዋል።

“ሽልማቱ በቀጣይ የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተነሳሽነትን የሚፈጥር ነው” ያሉት ደግሞ የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ምክትል ዳሬከተር አቶ ኮንግ ሬት ናቸው።

የእቅና ሽልማቱ ለ202 የፌዴራል፣ የክልልና የወረዳ የመንግስት ተቋማት፣ ለንግድና ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲሁም በመልካም ስራቸው ከፍተኛ አበርክቶ ለነበራቸው ግለሰቦች መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.