Fana: At a Speed of Life!

በካምፓላ የኢትዮጵያን የመስህብ ስፍራዎች የሚያስተዋውቅ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የኢትዮጵያን ድንቅ የመስህብ መዳረሻዎች ተዋወቁ’ በሚል ርዕስ በካምፓላ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት በበይነ-መረብ ውይይት ተካሄዷል።
በውይይቱ በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ኢትዮጵያና ኡጋንዳ የአባይ ውሃ መነሻ መሆናቸውን ጨምሮ የቱሪዝም ሀብቶችና ባህላዊ እሴቶች የሚጋሩ ናቸው ብለዋል።
በዚህም በዘርፉ ያላቸውን ትብብር በሚጠበቀው ደረጃ ለማሳደግ ተመሳሳይ መድረኮችን ማዘጋጀት፣ የመስህብ መዳረሻዎችን መለየትና የጋራ የቱሪዝም ጥቅሎችን ማቀናጀት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሃብቶችንና በዘርፉ ያለውን የኢንቨስትመንት እድል የሚያስተዋውቅ ገለፃ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.