Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዓለም አቀፍ ድጋፍ እያገኘ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዓለም አቀፍ ድጋፍ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ።
ኮሚሽኑ የሰብዓዊ መብቶችን የማስጠበቅ ተልእኮውን እንዲወጣ የጀርመን እና ዴንማርክ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለመደገፍ እንደሚሰሩ ተገልጿል።
ለኮሚሽኑ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ድጋፍ እየጨመረ መምጣቱ÷ በኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲ ለመሸጋገር የሚደረገውን ጥረት እና ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ግዴታዋን ለማክበር ለምታደርገው ጥረት አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም ጀርመን በዴንማርክ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም በኩል ሀብትን በማሰባሰብ እና ሁኔታዎችን በማመቻቸት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ለመደገፍ መወሰኗ÷ ኢሰመኮ ሙሉ ተቋማዊ አቅም እንዲያገኝ እና ለሰው ልጅ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ገለልተኛ እና ውጤታማ ድርጅት ለመሆን የሚያስችለውን መንገድ ለመክፈት ያስችለዋል ነው የተባለው።

 ከዚህ ባለፈም  የግለሰቦችን ቅሬታዎች መቆጣጠር እና አያያዝ እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ላይ ውጤታማ ስራ መሰራቱን  ከዴንማርክ የሰብዓዊ  መብቶች ተቋም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፡- የዴንማርክ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 5 people, people standing, suit and outdoors
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.