Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ኮሚዩኒስት ፖርቲ 100ኛ ዓመት ምስረታ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የኮሚዩኒስት ፓርቲን 100ኛ ዓመት ምስረታ በዓል እያከበረች ነው፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ንግግር ያደረጉ ሲሆን÷ ለመታሰቢያነትም 100 ጊዜ መድፍ መተኮሱ ተገልጿል፡፡

ዢ ጂንፒንግ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊ እና የፓርቲው ማዕከላዊ ሚሊተሪ ኮሚሽን ሊቀ መንበር እንደሆኑም ተመላክቷል፡፡

ፓርቲው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1921 ቼን ቱዡ በተባሉ የቻይና ሶሻሊስት አብዮተኛ መመስረቱ ይነገራል።
እስከ ፈረንጆቹ 2020 ድረስም ከ91 ሚሊየን ባላይ አባላቶች በማፍራት ከአሜሪካ ዴሞክራቲክ እና ሪፐብሊካን ፓርቲዎች ቀጥሎ በ2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ትልቅ ፓርቲ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ምንጭ፡ ሲ ጂ ቲ ኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.