Fana: At a Speed of Life!

ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 400 ሺህ  ኩንታል እህል በመቀሌ ማዕከላዊ መጋዘን ተከማችቷል – የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግስት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 400ሺ ኩንታል የምግብ እህልና አልሚ ምግቦች በመቀሌ ማዕከላዊ መጋዘን ማከማቸቱን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ ለመኸር እርሻ የሚሆን 617 ሺ ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ክልሉ ማስገባቱን አስታውቋል።

የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳና የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ÷ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የፌደራል መንግስት የትግራይ አርሶ አደር የእርሻ ጊዜውን በአግባቡ እንዲጠቀም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የቀረበለትን የተኩስ አቁም ውሳኔ መቀበሉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ዜጎች ድጋፉ

እንዳይቋረጥባቸው በመቀሌ ማዕከላዊ መጋዘን 400 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ የምግብ እህል ማከማቸቱን ኮሚሽነር ምትኩ ገልጸዋል።

በክልሉ ከመንግስት በተጨማሪ የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ያከማቹት የምግብ አቅርቦት መኖሩንም ገልጸዋል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ በበኩላቸው÷ በክልሉ ለመኸር እርሻ በቂ የግብርና ግብዓት ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት።

አርሶ አደሩ ራሱን በምግብ እንዲችልና ከድጋፍ እንዲላቀቅ ለማድረግ ከትራክተር ጀምሮ የማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦቶች መመቻቸታቸውንም ገልጸዋል።

በመቀሌ ማዕከላዊ መጋዘንም ከ368 ሺ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ መኖሩን አመልክተው÷ እስካሁን ወደ እርሻ ለገቡ 50 ወረዳዎች ውስጥ ለ40ዎቹ ማዳበሪያ መድረሱን አብራርተዋል።

የትግራይ ክልል በዓመት 55 ሺህ ሄክታር የሚያለማ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በተያያዘ ዜና የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ በትግራይ ክልል የሚገኙ የሰላም ሚኒስቴርና የሌሎች ተቋማት ሰራተኞችን ደህንነት ማረጋገጡን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቋል።

ኮሚሽኑ መቀሌ ከሚገኙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች ጋር በሚያደርገው የኢሜል ልውውጥ የሰራተኞቹን ደህንነት እየተከታተለ መሆኑን ኮሚሽነር ምትኩ ለኢዜአ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.