Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ለሚሳተፉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት እቅድ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ።
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የቦርድ አባላት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር በመሆን የህዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ሁኔታ ትናንት በቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል።
የግድቡ ግንባታ በተያዘለት ዕቅድ መሰረት እየተከናወነ ስለ መሆኑ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ተናግረዋል።
በግድቡ ግንባታ ሂደት ለሚሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች፣ የግንባታ አማካሪዎች እና በግድቡ ዙሪያ ድጋፍ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ምንጭ፡- ኢዜአ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.