Fana: At a Speed of Life!

“ክብር ለሀገር አንድነትና አብሮነት ለተሰው ጀግኖች” የውይይት መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)”ክብር ለሀገር አንድነትና አብሮነት ለተሰዉ ጀግኖች የመከላከያ ሠራዊት አባላት” በሚል መሪ ሃሳብ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከወጣቶች ጋር በአዲስ አበባ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተና ጄነራል ባጫ ደበሌ፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎችና በመዲናዋ የሚገኙ አርበኞች እንዲሁም ወጣቶች ተሳትፈዋል።

የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተተካ በቀለ በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ አገር ለማፍረስ እቅድ የነበረው የህወሓት ጁንታ ድል መደረጉን ገልጸዋል።

የጁንታው ኃይል ወደ መቐለ ያፈገፈገው በዴሞክራሲያዊ ሂደት ሽንፈት ገጥሞት መሆኑን አስታውሰው በዚህ ተስፋ በመቁረጡ አገር ለመበታተን ብዙ ጥረት ማድረጉን ጠቁመዋል።

“ሆኖም መንግሥት ባካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የጥፋት ቡድኑን እቅድ እንዳይሳካ ማድረግ ተችሏል” ብለዋል።

ዘንድሮ በተካሄደው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ወደሚፈለገው የዴሞክራሲ አቅጣጫ ጉዞዋን እንደምትቀጥል መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.