Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የስጋ ደዌ ቀን በኢትዮጵያ ለ21ኛ ጊዜ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም የስጋ ደዌ ቀን በኢትዮጵያ ለ21ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል።
 
ቀኑ “በእውቀትና በፍቅር የተመሰረተ ሁለንተናዊ አገልግሎት በመስጠት ከስጋ ደዌ ነፃ የሆነ ማህበረሰብ እንፍጠር” በሚል መሪ ቃል ነው ተከብሮ የዋለው።
በበዓሉም ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተ ሊያ ታደሰ፣ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ተወካዮች፣ የተጠሪ ተቋማት እና የሰራተኛና መህበራዊ ጉዳይ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
በዝግጅቱ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን የስጋ ደዌ ተጠቂዎች ሙሉ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ስራ ላይ የዋሉ ዋና ዋና የህግ ማእቀፎች አተገባበርና ተግዳሮቶች ዙሪያ የፓናል ውይይት ተደርጓል፡፡
 
ለስጋ ደዌ ዋናው ምክንያት በድህነት ምክንያት በቂ የጤና አጠባበቅ አገልግሎትን ካለማግኘት፣ ለጤና ተስማሚ የሆነ በቂ ምግብ ካለመመገብ ሲሆን በትንፋሽ የማይተላለፍ፣ በስጋ ዝምድና የማይተላለፍ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
 
ሥጋ ደዌ በሽታ በሁሉም የኑሮ ደረጃና በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወንዶችና ሴቶችን እኩል የሚያጠቃ ቢሆንም በይበልጥ የሚጠቁት በ15 እና በ 45 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ወይም በአምራች የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸው ይነገራል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.