Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመተባበር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰላምና ልማት ዙሪያ ለመተባበር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ።
በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ የተመራ ልዑክ ከኬንያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሊቀመንበር ቢሾብ ጆሰፍ ማታው ጋር ባደረጉት ውይይት በሰላምና ልማት ዙሪያ ለመተባበር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ችለዋል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑካን ቡድን በናይሮቢ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን የእምነት ተቋማት ተወካዮች ጋር ዛሬ በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውይይት ማድረጋቸው ተጠቁመዋል።
በናይሮቢ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቅርንጫፍ ለመመስረት አደራጅ ኮሚቴ መሰየሙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.