Fana: At a Speed of Life!

ለወላይታ ዲስትሪክት ጽ/ቤት አገልግሎት ህንፃ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለደቡብ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለወላይታ ዲስትሪክት ጽህፈት ቤት አገልግሎት ባለ ሰባት ፎቅ ህንፃ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
የመሰረት ድንጋዩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላና የደቡብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክንፈ ነጋሽ አስቀምጠዋል፡፡
ህንፃው ከ180 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ÷በአገሪቱ ዲስትሪክት ባለባቸው ስድስት ከተሞች ተመሳሳይ ስራዎች እንደሚሰሩም ተጠቁሟል፡፡
በጌትነት ጃርሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.