Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ ነዋሪዎች አሸባሪው ህወሓትን የሚቃወምና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

 

በድጋፍ ሰልፉ ላይም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር  ወይዘሮ  ሚስራ አብደላ ፣  የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ  ጽሕፈት ቤት ሀላፊ  አቶ አብዱ ጀባር መሀመድን ጨምሮ  የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣  የሀይማኖት አባቶች ፣ ሀገር ሽማግሌዎች እና አባገዳዎች ተገኝተዋል።

 

በአሁኑ ሰዓት መከላከያ ሰራዊታችን የኢትዮጵያ ጠላት የሆነው አሸባሪው ህወሓትን ለመደምሰስ ፣  የሀገራችን ሰላም በእጃችን መሆኑን ለአለም ህዝብ ለማሳየት እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት ለመደገፍ እና ከጎናቸው መሆናቸውን አቶ ኦርዲን ተናግረዋል፡፡

 

ነዋሪዎቹ ባካሄዱት  ሰልፍ ላይም  “እኛ የመከላከያ ደጀን ነን!” ፣  “የመከላከያ ሰራዊታችን ተከፍሎ የማያልቅ ውለታ አለብን!” ፣  “የኢትዮጵያን ክብር አሳልፎ የሚሰጥ ትውልድ የለም!” ፣  “የጦር መሣሪያ ከትግራይ ሕፃናት ትከሻ ይውረድ!” ፣  “የህወሃት ጁንታ ቡድን የኢትዮጵያ ጠላት ነው!”  የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችም ተላልፎበታል።

 

ለጀግናው  የሀገር መከላከያ ሰራዊት  የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በመዘርዘር የድጋፍ ሰልፉ ተጠናቋል ።

በነስሪ ዩሱፍ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.