Fana: At a Speed of Life!

ለበረራ ኢንዱስትሪው መፍትሄ የሚሆኑ የፈጠራ ስራዎችን ለማልማት የሚያስችል የዲጂታል ስርዓት ሊዘረጋ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ ኢንዱስትሪው መፍትሄ የሚሆኑ የፈጠራ ስራዎችን ለማልማት የሚያስችል የዲጂታል ስርዓት ከመጭው ነሃሴ ጀምሮ ሊዘረጋ ነው።

አየር መንገዱ ዲጂታል ስራ ፈጠራና ኢኖቬሽን በሚል በተካሄደው የዲጂታል ኢትዮጵያ ተከታታይ የበይነ መረብ ውይይት አካል በሆነው መድረክ ላይ ነው ይህንን ይፋ ያደረገው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቢዝነስ ዲቨሎፕመንትና የኢኖቬሽን ሃብ መስራችና ዳይሬክተር አቶ ዐቢይ አስራት አየር መንገዱ አጋሮቹ የሚሳተፉበትና ለበረራ ኢንዱስትሪው መፍትሄ የሚሆኑ የፈጠራ ስራዎችን ለማልማት የሚያስችል የዲጂታል ስርዓት ከመጭው ነሃሴ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

አጋሮች የፈጠራ ሃሳቦቻቸውን የሚያለሙበት፣ የሚያሳድጉበትና ወደ ምርትና አገልግሎት የሚያውሉበት ስርዓት እንደሚዘረጋና ይህንንም አየር መንገዱ በገንዘብ የሚደግፍበት ስርዓት እንደሚመቻች ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.