Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ያሰለጠናችውን 397ሠልጣኞች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በወንጀል ምርመራና በመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ያሰለጠናችውን 397 ሠልጣኞችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የከተማውን ሰላምና ፀጥታ መጠበቅ የሚችል የፖሊስ ሀይል በመፍራት ላይ እንገኛለን ሲሉ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡
ላለፉት አመታት በወንጀል ምርመራና በመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር እያጋጠሙ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የዛሬ ተመራቂዎች እገዛ ያደርጋሉም ብለዋል፡፡
የትራፊክ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ጉዳት ለመቀነስ ተመራቂዎች ጠንክረው በመስራትና ከአድሎአዊ አሰራር በመራቅ ህብረተሰቡን ማገልገል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
በአሁኑ ወቀት አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን በህዝቡና በሰራዊቱ ላይ እየፈፀመ ያለውን የሽብር ተግባር በመመከት የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ርብርብ ማድረግ ይኖርበታል ማለታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.