Fana: At a Speed of Life!

ህንድ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ያሳየችውን ድጋፍ ኢትዮጵያ ታደንቃለች-አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ህንድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ ለመወያየት በተጠራው ስብሰባ ላይ ያሳየችው በመርህ ላይ የተመሰረተ አቋም የሚደነቅ መሆኑን በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ አስታወቁ።
አምባሳደሯ ኢትዮጵያና ህንድ ጠንካራ እና ለረዥም ዓመታት የቆየና ግንኙነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን ዊኦን ከተባለ መገኛና ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።
የሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸው ከ70 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም የኢትዮጵያና ህንድ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመምጣቱም ባለፈ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በባህል ግንኙነት ያላቸው ሁኔታም እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።
ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞም ባለፈው መጋቢት ወር ህንድ ለኢትዮጵያ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የኮቪድ 19 ክትባት መለገሷን አስታውሰዋል።
አምባሳደር ትዝታ በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታም አብራርተዋል።
በክልሉ ችግሩ የሽብርተኛው ቡድን ባለፈው ጥቅምት 24 የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ባጠቃበት ወቅት መከሰቱን ተናግዋል።
በዚህም መንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻም ማካሄዱን ገልጸዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ሐምሌ 2 ቀን ላይ በተሰበሰበበት ወቅት፥ በተመድ የህንድ ተወካይ የሆኑት ትሩሙርቲ የአንድን ሀገር ሉዓላዊነት በመጠበቅ በመርህ ላይ የተመሰረተ አቋም ማንጸባረቃቸውን ተናግረዋል።
በወቅቱም ተወካዩ መንግስት በትግራይ ክልል የተናጥል የሰብአዊ የተኩስ አቁም ማወጁን እና በብዙ ውጥረት ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን መስራቱ ምስጋና ይገባዋል ማለታቸውን አምባሳደሯ አስታውሰዋል።
አምባሳደሯ አያይዘውም ህንድ የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት የማክበር እና በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ አለመግባት በመርህ ላይ የተመሠረተ አቋም ነበራት በዚህም ኢትዮጵያ ያላት ን አድናቆት ገልጸዋል።
በዚህ ዓመት መጀመሪያ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶደመቀ መኮንን ህንድን የጎበኙ ሲሆን ፥ ከህንድ አቻቸው ኢኤም ጃይሻንካር ጋር በነበራቸው ውይይትም በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውንም አስታውሰዋል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
55
Engagements
Boost Post
52
3 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.