Fana: At a Speed of Life!

ዩጋንዳ ከ50 በላይ የሚሆኑ ሲቪክ ማህበራትን ፈቃድ አገደች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩጋንዳ ከ50 በላይ የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ፈቃድ ማገዷ ተሰምቷል፡፡

ሲቪክ ማህበራቱ የታገዱት መንግስት ያወጣቸውን ደንቦች እና አሰራሮች በመጣሳቸው መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ድርጅቶቹ ውል የገቡበት የሥራ ጊዜ ከመጠናቀቁ ባለፈ አስፈላጊውን የምዝገባ ሂደት ጠብቀው የሥራ ፈቃድ ከሚሰጥ አካል ፈቃድ አለማግኘታቸውም ተመላክቷል፡፡

ፈቃዱ ከታገደባቸው ሲቪክ ማህበራት መካከል በሰብዓዊ መብቶች እና በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ኤጀንሲዎች እንደሚገኙበት ጉዳዩን የሚከታተለው የሀገሪቱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጽህፈት ቤትአስታውቋል፡፡

ዕገዳውን ተከትሎም በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ የድርጅቱ ሰራተኞች ለችግር ተጋለጭ ሊሆኑ አንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡ ይህ የመንግስት ውሳኔም በሀገሪቱ የሚስተዋሉ የመብት ጥሰቶች ተባብሰው እንዲቀጥሉ ያደርጋል የሚል ስጋት አጭሯል፡፡

ምንጭ÷ አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.