Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶ ከተማ ህወሓትና ሸኔን የሚቃወም ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔን የሚቃወም እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በዚሁ ወቅት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በስነ ልቦና ሊበጠስ በማይችል አንድነት የተሳሳሩ ብሄረሰቦች ያሉባት ሀገር ናት ብለዋል።
ስግብግቡ፣ ከፋፋዩና ዘረኛው አሸባሪው የህወሓት ቡድን የዛሬ 30 ዓመት የተከለው ክፉ ዘር ሀገራችንን ዋጋ እያስከፈላት ይገኛልም ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያዊያን ይህንን ወቅት በአንድነት፣ እና በሰከነ ልቦና በማየት ሀገራችንን ወደ ድል መምራት ይጠበቅብናል ማለታቸውንም ደሬቴድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.