Fana: At a Speed of Life!

የንግዱ ማህበረሰብ የገበያ ዋጋን በማረጋጋት የመልካምነት አርዓያ መሆን ይጠበቅበታል- የሐረሪ ክልል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ በክልሉ ከሚገኙ የደቡብ ክልል ተወላጆች እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የክልሉ መንግሥት በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ የመሰረተ ልማት እና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም ተያያዥ ችግሮችን ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በአሁኑ ወቅት የንግዱ ማህበረሰብ በአገሪቱ ላይ ከውስጥና ከውጭ የተቃጣውን ሀገር የማፍረስ ሴራና ኢኮኖሚያዊ አሻጥርን እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለይ በአሁኑ ወቅት መንግስትን እና ህዝቡን እየተፈታተነ የሚገኘውን የዋጋ ንረትን በማረጋጋት በኩል የንግዱ ማህበረሰብ የራሱን አስተዋፅኦ በማበርከት “የመልካምነት” ዓርዓያ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ነጋዴዎች በበኩላቸው በክልሉ የዋጋ ንረትን በመፍጠር አሻጥር የሚሰሩ የመንግስት ተቋማትንም ሆነ ስግብግብ ነጋዴዎችን የማጋለጡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በተለይ በአሁኑ ወቅት ሃገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ በመገንዘብ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚቀጥሉና በቀጣይም እስከ ግንባር ድረስ በመሄድ ለሰራዊቱ አለኝታነታቸውን ለማሳየት እየተዘጋጁ ስለመሆኑን መናገራቸውን ከሐረሪ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የተገነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.