Fana: At a Speed of Life!

በ70ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸው ወቅት የ768 ሺህ ሎተሪ አሸናፊ የሆኑት ጥንዶች  

አዲስ አበባ፣ጥር 26፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜን ካሮላና ነዋሪ የሆኑት ጥንዶች የ70ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን በሚያከብሩበት ወቅት የ768 ሺህ 862 ሎተሪ አሸናፊ መሆናቸው ተሰምቷል።

ጥንዶቹ በደረሳቸው የሎተሪ ዕጣም የ70 ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን በመርከብ ሽርሽር እና በተለያዩ ቦታዎች ራሳቸውን ለማዝናናት ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ሚስት ማክሲ ሂልከር ይህንን የሎተሪ ጨዋታ በካሊፎርኒያ፣ ፍሎሪዳ እና አሁን ደግሞ በሰሜን ካሮላይና ውስጥ ከ 22 ዓመታት በላይ መጫወታቸውን አስታውሰዋል።

ሁሌም ማክሰኞ ማክሰኞ ወደ ተመሳሳይ መደብር  በመሄድ  የእርሳቸውን፣ የባለቤታቸውን እና የሶስት እህቶቹን ልደት  ቁጥር በመጠቀም  ተመሳሳይ ቁጥሮች በምግዛት እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።

ባል ጄምስ ሂልኪር  በበኩላቸው  የሎተሪ አሸናፊ የሆኑበት ቁጥርን ሰኞ ማለዳ ማወቃቸውን በመግለጽ እስከ  ሰኞ ረፋድ በጋዜጣ እስኪወጣ ድረስ ለባለቤቱ  አለማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡

ጥንዶቹ  የሎተሪ ዕድሉ የጋብቻ በዓላቸውን በሚያከብሩበት ወቅት መውጣቱ ይበልጥ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

ምንጭ፡-https://www.upi.co

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.