Fana: At a Speed of Life!

በውስጥና በውጭ የተጋረጡ ችግሮችን ለማለፍ በጋራ መቆም ያስፈልጋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደ ሀገር በውስጥም በውጭም እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለማለፍ በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሔል ባፌ ገለጹ፡፡

ሰብሳቢዋ አሁን ካለው ሃገራዊ ሁኔታ አንጻር መደማመጥ፣ መነጋገርና በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግም ነው የገለጹት።

የውስጥ ችግሮችን በተቻለ ፍጥነት በመፍታትና በአንድነት በመቆም የሚመጡ የውጭ ጫናዎችን በጋራ መመከት ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡

መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በተመሰረተው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት እንዲካተቱ መደረጉ የተለያዩ ሀሳቦች እንዲደመጡ እና አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተሻለ መግባባት እንዲኖር ያደርጋል ማለታቸውን ኢ ፕ ድ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.