Fana: At a Speed of Life!

የጤና ስርዓቱ ለማህበረሰቡ ምላሽ ሰጪ እንዲሆን ይሰራል- ዶክተር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጤና ስርዓቱ ለማህበረሰቡ ምላሽ ሰጪ እንዲሆን ይሰራል ሲሉ የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
ሚኒስትሯ ይህን የገለጹት በጅጅጋ እየተካሄደ ባለው 23ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤ ላይ ነው።
ኮቪድን ጨምሮ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያለፈ ያለው የጤና ሴክተሩ በ2013 እምርታዊ ለውጥ የታየባቸው ስራዎች መከናወናቸውን ዶክተር ሊያ አንስተዋል።
በቀጣይነትም ጥራት እና ፍትሃዊነት ያለው የጤና ተደራሽነት ፣ ተነሳሽነት እና ርህራሄ ያለው የጤና ባለሞያ በሚፈለገው ደረጃ እንዲኖር እንዲሁም ዘላቂነት ያለው የጤና ፋይናንስ እንዲኖር ይሰራልም ብለዋል ሚኒስትሯ።
ጥራት ያለው የጤና መረጃን መስጠትም በትኩረት የሚሰራበት ይሆናልም ነው ያሉት።
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን በበኩላቸው ፥ መንግስት ለጤናው ዘርፍ የሠጠው ትኩረት ከሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም ከጤና ባለሞያዎች ርብርብ ጋር ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አንስተዋል።
በቀጣይም የእናቶች እና ህፃናት ጤና ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በመድረኩ የተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች በጤናው ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ ለውጥ እና የስራ ትጋት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በጉባኤው ሚኒስትር ድኤታዎች፣የክልል የስራ ሀላፊዎች እና ለሎች ባለድርሻ አካላት እና ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ሲሆን ጉባኤው በነገውም እለት የሚቀጥል መሆኑ ተመላክቷል።
አፈወርቅ አለሙ እና ፈቲያ አብደላ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግ
+3
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.