የአማራ ክልል ፖሊስ ያሰለጠናቸውን የልዩ ሃይል አባላት አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለማዳን የአማራ ክልል መንግስት ያወጀውን የክተት ጥሪ ተቀብለው ስልጠና የወሰዱ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ዛሬ ተመርቀዋል፡፡
በምረቃ ስነ ስዓቱ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀምበር፣ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ሁልጊዜም ሀገርንና ህዝብን የሚያስቀድመው የአማራ ልዩ ሃይል ከመከላከያ፣ ከሚሊሻ እና ፋኖ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚል ከንቱ ቅዠት ተነስቶ አማራንና አፋርን መውረር የጀመረውን የትግራይ ወራሪ ቡድንን ለመቅበር በከፍተኛ ወኔና እልህ መነሳቱ ተመላክቷል፡፡
ሁሉም አካል በመተባበርና በአንድነት በመትመም ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ ወራሪውን ለመቅበር መነሳት እንዳለበት ጥሪ መቅረቡን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!