Fana: At a Speed of Life!

በጦርነት የተጎዱ ሀገራት በቻይና ገበያ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 30፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በምዕራባዉያን ጫና ምክንያት በጦርነት የተጎዱ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በቻይና ገበያ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ።
ቻይና በምዕራባውያን ጫና በጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸዉ ሀገራት ጋር የንግድ ተስስርን በመፍጠር የሀገራቱ ኢኮኖሚ እንዲያገግም አስተዋፅኦ እያደረገች መሆኑ ተገልጿል።
በአፍጋኒስታን በንግድ ስራ የተሰማራው አሊ ፊያዝ ባለፈው አመት በቻይና የኢንዱስትሪ መሐንዲሶች ተቋም ላይ በአባልነት መስራት ከጀመረ በኋላ የሚያቀርባቸዉ ምርቶች በቻይና ደንበኞቹ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኙ መምጣታቸዉን እና በሚያገኘዉ ገቢም የአፍጋኒስታን ያሉ ወገኖቹን እየረዳ መሆኑነ ተናግሯል።
በተመሳሳይም ሌላኛዋ የመካከለኛዉ ምስራቅ ሀገር ሶሪያ ዜጎች ከቻይና ጋር ያላቸዉን የንግድ ግንኙነት እያጠናከሩ መሆኑ ተገልጿል።
የሶሪያ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ለሱፍ ማምረቻ የሚያገለግሉ ጥሬ ቃዎችን ለቻይና መላክ የጀመሩ ሲሆን፥ የ100 ዓመታት ታሪክ ያለው እና በሶሪያ የሚገኘው ዳካ ካዲማ ፋብሪካ ምርቶቹን ወደ ቻይና እየላከ መሆኑ ተገልጿል።
የቻይና የኢንዱስትሪ መሐንዲሶች ተቋም ከ127 አገሮች እና ክልሎች የተውጣጡ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ኩባንያዎችን አሳታፊ አድርጓል።
33 ያደጉ አገሮችን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ኩባንያዎችን በማካትት እና ወደ ሰፊው የቻይና ገበያ የሚላኩ ምርቶችን በማሳደግ ትልቅ የንግድ መድረክ ይፈጥራል ሲል ዥንዋ በዘገባዉ አስታዉቋል።
በሚኪያስ አየለ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.