የ12ኛ ክፍል ፈተና ይፈተናሉ ከተባሉ ተማሪዎች 96 ከመቶ በላይ በመፈተን ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ።
የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በኢትዮጵያ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ፈተናው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተናግረዋል።
በዚህ አመት በ2 ሺህ 36 የፈተና ጣቢያዎች በተሰጠው ፈተና ÷ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ከታሰበው 617 ሺህ 991 ተማሪዎች ውስጥ 565 ሺህ 255ቱ ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል።
ይህም የዕቅዱን 96ነጥብ 5 በመቶ የያዘ ነው።
ኢትዮጵያ በፈተናዎች ውስጥ ሆና ተማሪዎችን መመዘን መቻሏ እንደስኬት የሚታይ እንደሆነም ነው የተነሳው።
ለዚህም ከፀጥታ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር የተሰራው ስራ ውጤት አስመዝግቧል ተብሏል።
በፈተናው ወቅት ከኩረጃ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በፍጥነት እርማት ተሰጥቷል ያሉ ሲሆን ÷ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ ደግሞ ለማጣራት ጊዜ ተወስዶ ይፈታል ብለዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ የነበሩ እንቅስቃሴዎችንም በቴክኒካል ኮሚቴ ተጣርቶ እርምጃ ይወሰዳልም ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ።
የደረሱ ጥቆማዎችን አጣርቶ በውጤት ትንተናና በሪፖርቶች ላይ ጥናት መሰረት ተወስዶ የሚወሰድን ውሳኔ ወደፊት ይፋ ይደረጋልም ብለዋል።
በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ፈተና ያልተሰጠባቸው አካባቢዎች ለተማሪዎቹ የስነ ልቦና ግንባታ ስራ ተሰርቶ በሁለተኛ ዙር በመፈተን ከመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ነው የተጠቀሰው፡፡
በአፈወርቅ እያዩ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!