Fana: At a Speed of Life!

የሽብር ቡድኑ ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ህዝቡ እያደረገ ያለውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 04 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ህዝቡ እያደረገ ያለውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሀላፊ ሚኒስትር ዶር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፥ የሽብር ቡድን ወረራ በፈፀመባቸው በዋግ ኸምራ ሰሜን ወሎ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች የአካባቢው ማህበረሰብ ራሱን በማደራጀት ወራሪው ይዟቸው የነበሩ አካባቢዎችን እንደገና አስመልሶ በቁጥጥሩ ስር እያዋለ ይገኛል ብለዋል።
መንግስት ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ እና አኩሪ ተግባር እንደሚደግፍና እንደሚያደንቅ ሚኒስትሩ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የህወሃት የሽብር ቡድኑ ከሸኔ ጋር ጥምረት በመፍጠር ያደረገውን እንቅስቃሴ የኢፊዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከልዩ ሐይል፣ ፍኖ፣ ሚኒሻና ከህዝቡ ጋር በመሆን በወሰደው ፀረ ማጥቃት ከፍተኛ ኪሳራ ደረሶበት በከሚሴ ከበባ ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለው እረምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጽው፥ ለዚህም የኦሮሚያ ወጣቶች እና ህብረተሰቡ ላሳየው ትብብር ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ የሀገር ሉአላዊነትን ለማስከበር ባደረገለት ጥሪ መሰረት ባለፉት ሁለት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በርካታ ወጣቶች የመከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል ያሳዩበት ሳምንት እንደነበርም ነው ያስረዱት።
በሀገራችን ላይ ከውጭ ሚዲያዎች የሚደርሰውን የሀሰት ወሬ መላው የኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ሰልፍ በመውጣት አውግዘውታል፤ የህዝቡ ድምፅ ሊከበር ይገባል ሲሉም ዶክተር ለገሰ በመግለጫቸው አንስተዋል።
ዶር ለገሰ አክለውም፥ የአሜሪካ መንግስት በኤርትራ የጦር መኮንኖች ላይ የጣለውን መዕቀብ እንደገና ሊያጤነው ይገባል ብለዋል።
ህብረተሰቡ በየአካባቢው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
በምንይችል አዘዘው
አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.