Fana: At a Speed of Life!

የብቸኝነት ስሜት በጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያስከትል ይችላል-ጥናት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስር የሰደደ ብቸኝነት ስሜት በጤንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያስከትል አንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።

ሁሉም ሰው በሆነ ወቅት ላይ የብቸኝነት ስሜት ሊሰማው የሚችል ሲሆን፥ ለአንዳንድ ሶዎች ደግሞ ብቸኝነት የህይወት ዘይቤያቸው ነው፤ ይህም በዙሪያቸው ሰዎች በማጣት ሳይሆን ከሰዎች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ችግር ስላለው መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል

አዲስ አካባቢ በመሄድ፣ አዲስ የስራ ቦታ ሲገቡ የብቸኝነት ስሜት ለያጋጥም ይችላል የሚለው ጥናቱ፥ ይህ ግን በብዙዎች ዘንድ ጊዜያዊ መሆኑንም ይገልፃል።

ጥናት እንዳመለከተው ስር ሰደደ የብቸኝነት ስሜት በጤናችን ለይ መጥፎ ውጤት ሊያስከትል የሚችል ሲሆን፥ ባለፉት ዓመታት በጥናቱ የተለዩ ግኝቶች ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ይመስላሉ።

  1. ከአካላዊ ህመም ጋር ተመሳሳይ በሆነ መንገድ አንጎልን ሊጎዳ ይችላል

የማህበራዊ ግንኙነታቸው ከፍ ካሉ ሰዎች ይልቅ በከባድ የብቸኝነት ስሜት ውስጥ ያሉ ሰዎች የጭንቀት የሆርሞናቸው ጠዋት ጠዋት ከፍ ብሎ መገኘቱን ጥናቱ አመልክቷል።

ቢሆንም ተመራማሪዎች በአዕምሯዊና አካላዊ ሁኔታዎች ላይ የብቸኝነት ስሜት  የሚፈጥረው ተጽዕኖ ተያያዥነቱን በመመርመር ላይ   መሆናቸውን ገልጸዋል።

  1. ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ እንዳያገኙ ሊያደርግ ይችላል

የብቸኝነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች በሌሊት የበለጠ የእንቅልፍ መዘበራረቆች እንደሚያጋጥማቸው ተገልጿል።

በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉት 95 በመቶ የሚሆኑት ተሳታፊዎች ሁሉም ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነቶች ነበራቸው ሲሆን፥ የብቸኝነት መጠናቸው አነስተኛ ልዩነቶች እንኳ በእንቅልፍ የሚያስከትለው ጫና ተስተውሏል።

  1. የመርሳት ችግርን ሊያስከትል ይችላል

በአውሮፓውያኑ በ2012 በአመስተርዳም ለሚኖሩ ወደ 2 ሺህ 200 የሚጠጉ አዛውንቶችን ላይ በተደረገ ጥናት በዙሪያቸው ያሉ ጓደኞች እና ቤተሰቦች ብዛት ምንም ይሁን ምን ፣ ብቸኝነት የሚሰማቸው ተሳታፊዎች  በአዕምሮ የመርሳት በሽታ የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አመላክቷል።

እንደ ዕድሜ ያሉ ምክንያቶች ከተስተካከሉ በኋላ የብቸኝነት ስሜት 64 በመቶ የመርሳት ችግርን ከፍ እንደሚያደርግ ጥናት ማመላከቱን  ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።

  1. ያለጊዜው ለሚከሰት ሞት አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይችላል

በፈረንጆቹ በ2012 የተደረጉ ሌሎች ጥናቶች እንዳሳዩትእንድ ሰው ብቸኛ መሆን – ወይም  ብቸኝነት የሚሰማው ከሆነ ቀደም ብሎ  ለሚከሰት ሞት የመጋለጥ  እድሉ ከፍ ሊያደርግ ይችላል ተብሏል።

  1. የልብ ህመምን ሊያስከትል ይችላል

በአውሮፓውያኑ 2011 በ93 ጎልማሳዎች  ላይ የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው በከባድ የብቸኝነት ስሜት ውስጥ ያሉ ሰዎች ከመጠን በላይ መጨናነቅ  ህብረ ህዋሳትን ከመጉዳቱም ባሻገር ሲቆይ ወደ ልብ ህመምና ካንሰር ሊያመራ ይችላል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-ሲ.ኤን.ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.