Fana: At a Speed of Life!

ለተፋሰሱ ሀገራ የሚጠቅመው በትብብርና በመተጋገዝ መስራት ብቻ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአባይ ጉዳይ ለተፋሰሱ አገሮች የሚጠቅመው በትብብርና በመተጋገዝ መስራት ብቻ ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ መሀመድ አል አሩስ ገለጹ።
መሀመድ አል አሩስ እንደገለጹት÷ የአባይ ጉዳይ በትብብርና በመተጋጋዝ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ተባብረው በመስራት ፍትሃዊ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል አመላክተዋል፡፡
ግብጽ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ኢትዮጵያ እንዳትገነባ በተለያየ መልኩ ስትጥር እንደነበረ አስታውሰው÷ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያ ደካማና ያልተረጋጋች ሀገር ሆና እንድትቀጥል ፍላጎቷ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
የግብፅ ባለስልጣናት ከድሮ ጀምሮ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባትና ምስራቅ አፍሪካን በማዳከም በቀጠናው የራሳቸውን ጥቅምና ፍላጎት ለማሟላት ሲንቀሳቀሱ መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡
የግብጾች ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያ ከበለጸገችና ከለማች፣ በኢኮኖሚውና በፖለቲካው ዘርፍ በአፍሪካ ኃያል ትሆናለች ከሚል ስጋት የመነጨ መሆኑንም አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ የግብፅን መገዳደርና ጣልቃ ገብነት በመታገል በሯሷ ሃብት የመበልጸግ መብቷን ማረጋገጥ አለባትም ብለዋል፡፡
የግብፅ ለቀጠናው የማይጠቅምና ግብፅ በአለም አቀፉ የፖለቲካ መደላድል ውስጥ ያላትን ተቀባይነት ገደል የሚከት መሆኑን ጠቁመው÷ ለሶስቱ የተፋሰሱ አገሮች የሚጠቅመው ጉዳይ በትብብርና በመተጋገዝ መስራት ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ደጋግማ እንደምትገልጸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተፋሰሱ አገሮች ላይ ጉዳት እንደማያደርስ የታወቀ ቢሆንም÷ ግብፅ ግን ጉዳዩን ፖለቲካዊና አለም አቀፋዊ የክርክር ምንጭ በማድረግ ግንባታውን ለማስተጓጎል ያለ እረፍት እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።
ከ86 በመቶ በላይ የአባይ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የምትገነባው በጨለማ ውስጥ እየኖረ ካለው በርካታ ህዝቧ ጥቂቱንም ቢሆን ብርሃን እንዲያገኝ ለማድረግ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.