Fana: At a Speed of Life!

ሀገር የማፍረስ ዓላማን ያነገቡ አሸባሪዎች እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ መስራት ይገባል- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር የማፍረስ ዓላማን ያነገቡ አሸባሪዎች ከአገር ውስጥ እና ከውጭ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ በጠንካራ ትብብር መስራት እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ።

ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት ዛሬ “ዲፕሎማሲያችንን በአዲስ ምዕራፍ ለላቀ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል የሚሲዮን መሪዎችና የዋናው መስሪያ ቤት የስራ ኃላፊዎች ዓመታዊ ስብሰባ ሲጀመር ነው።

ሀገርን ለማፍረስ እና ለማተራመስ እየተደረገ ያለውን የአሸባሪዎችና የተባባሪዎቻቸውን ተልዕኮ ለማምከን በዲፕሎማሲው ዘርፍ ብዙ ሥራ እንደሚጠበቅ አምባሳደር ሬድዋን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተቋማዊ ለውጥና አገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸምን ለማሳደግ ከዚህ በፊት በተቋሙ ሥራ ላይ እንዲዉሉ የተደረጉና ወቅታዊ ያልሆኑ መመሪያዎችን በማሻሻል፣ የአደረጃጀት ክፍተቶችን በመለየት፣ ተቋማዊ ሪፎርም ከታህሳስ 2013 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን አብራርተዋል ።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሲሰራበት የቆየው የለውጥ ሥራ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገው የለውጥ ሥራ አንዱ አካል መሆኑን እና አሁናዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን ማከናወን እንዲያስችል ተደርጎ የተቀረጸ ስለመሆኑም አንስተዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.