Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው የኦሮሚያ ክልል የአቃቤ ህጎች አጠቃላይ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው የኦሮሚያ ክልል የአቃቤ ህጎች አጠቃላይ ጉባኤ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዱኛ አህመድ የክልሉ አቃቤ ህግ ቢሮ ስለ ህግና የፍትህ ስርአት ግንዛቤ ለመፍጠር፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ የወንጀል ህግን ተፈፃሚ ለማድረግና የህዝብና የመንግስትን ጥቅም ለማስጠበቅ እንደተቋቋመ ተናግረዋል።

በመሆኑም እየተደረገ ያለው ጉባኤ የአቅቤ ህጎችን አቅም በማጎልበት ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ያደርጋልም ነው ያሉት።

በጉባኤው ላይ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን “ሃገራዊ ምክክርና የሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ” የሚል ፅሁፍ ቀርቦ ምክክር እየተደረገበት ይገኛል።

በሙክታር ጠኃ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.