Fana: At a Speed of Life!

ሁዋዌ ከሌሎች ኩባንዎች በተለየ በቻይና መንግስት ድጋፍ እንደማይደረግለት ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁዋዌ ከቻይና መንግስት ጋር ከሌሎች ኩባንያዎች የተለየ ግንኙነት እንደሌለው አስታወቀ።

ኩባንያው ከቻይና መንግሥት በኩል ከሌሎች ኩባንያዎች በተለየ መልኩ ድጋፍ ይደረግለታል መባሉን አስተባብሏል።

ወል ስትሪት ጆርናል ኩባንያው በተለያዩ መንገዶች ከቻይና መንግስት እስከ 75 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለታል የሚል መረጃ ይዞ ወጥቷል።

ኩባንያውም ከሌሎች በተለየ መልኩ ከመንግስት ድጋፍ እንደማይደረግለት በመግለጽ የወጣውን መረጃ አስተባብሏል።

ከዚህ ባለፈ ግን ቻይና ውስጥ እንደተሰማሩት ሌሎች ኩባንያዎች ከመንግስት በኩል ህጋዊ የፖሊሲ ድጋፍ ብቻ አገኛለሁ ነው ያለው።

ሁዋዌ የወል ስትሪት ጆርናልን ዘገባ መሰረተ ቢስ በማለት ለቀረበበት ስም ማጥፋት ህጋዊ መንገድ እንደሚከተልም ገልጿል።

ምንጭ፡-ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.