Fana: At a Speed of Life!

ለህወሓት የሽብር ቡድን ድጋፍ ሊውል የነበረ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ተያዘ  

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ)  በህገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ የነበረ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ብር ተያዘ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንዳስታወቀው፥ ገንዘቡ በህብረተሰቡ ጥቆማ እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተይዟል።

ከህገወጥ ገንዘብ ዝውውሩ ጋር ታያይዞም የውጪ ሀገር ዜግነት ያለው ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ነው ፖሊስ ያመለከተው።

ተጠርጣሪው ገንዘቡን በኢንቨስትመንት ሽፋን ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ ለማስገባት ቶዮታ በተለምዶ ዶልፊን ተብሎ በሚጠራ ተሽከርካሪ በኋላ ፍሬቻና በተለያዩ የመኪናው አካል ክፍሎች ደብቆ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል።

ፖሊስ በመጀመሪያ ደረጃ ምርመራው ገንዘቡ በትግራይ ክልል ለሚንቀሳቀሰው አሸባሪ የህወሓት ቡድን እኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ ሊውል እንደነበር ማወቁን ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.