Fana: At a Speed of Life!

ለወባ በሽታ መከሰት ምቹ የአየር ሁኔታ በመኖሩ በሽታው በሚከሰትባቸው አካባቢዎች የሚኖር ህብረተሰብ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል- የጤና ሚንስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጪ ወራት ለወባ በሽታ መከሰት ምቹ የአየር ሁኔታ በመኖሩ በሽታው በሚከሰትባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የጤና ሚንስቴር አሳሰበ።

የሚንስቴሩ የብሄራዊ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ መብራህቶም ሃይለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ትንበያን መሰረት በማድረግ ዝናባማ የአየር ጠባዩ እስከ መስከረም አጋማሽ ሊቆይ ስለሚችልና ይህም ለወባ ትንኝ መፈልፈያ የሚሆኑ የተቋጠሩ ውሃዎችን ሊፈጥር ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ አስገንዝበዋል።

አሁን ላይም ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ቤቶች ላይ የኬሚካል ርጭት ለማድረግ ታቅዶ ከግማሽ ሚሊየኑ መከናወኑን ነው ሚንስቴሩ ያስታወቀው።

ሚንስቴሩ በክልሎች የሚነሳው የጸረ ወባ የኬሚካል ግብዓት አቅርቦት እጥረት በአለም አቀፍ ገበያው ላይ የተከሰተ እና የወባ ትንኝ ኬሚካሉን የመላመድ አዝማሚያ በታቀደ መልኩ ከኬሚካል መጠቀም ወደ አጎበር መጠቀም እየተገባ በመሆኑ የተፈጠረ ነው ብሏል።

በ2012 በጀት አመት 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎች በወባ በሽታ ተይዘው፤ 213 ሰዎች በዚሁ በሽታ ህይወታቸው አልፏል።

በተለይም ሰፋፊ እርሻዎች ባሉባቸው አካባዎች ላይ የወጣ በሽታ እንዳይከሰት እና ቢከሰተም እንኳን በፍጥነት ለማከም እንዲያስችል ተንቀሳቃሽ እና ጊዜያዊ የህክምና አገልግሎት መስጫዎች እየተቋቋሙ ነው ብለዋል የሚንስቴሩ የብሄራዊ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ መብራህቶም ሃይለ።

በምስክር ስናፍቅ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.