Fana: At a Speed of Life!

ለወንድሜ ዐቢይ አህመድ እንኳን ደስ አለህ – ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንኳን ደስ አለህ ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ከአሁን ቀደም ኢትዮጵያ ለሱዳን ችግሮች ፈጥኖ ደራሽ ሃገር እንደነበረች አንስተው ፤ በአሁኑ ወቅትም ወዳጅነቷ የቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የትም ቦታ የትም ብትሆኑ አብሪያችሁ ነኝ ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ እዚህ የመጣሁት የኢትዮጵያን ህዝብ ሰላም ለማለት እና ወንድሜ ዐቢይን እንኳን ደስ አለህ ለማለት ነው ብለዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጎን እንድትሆኑ እጠይቃለሁም ነው ያሉት፡፡

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ማርዲያት ለዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያን እና የደቡብ ሱዳን የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ጠቁመው÷ በደቡብ ሱዳን የተረጋጋ ሁኔታ መፈጠር የኢትዮጵያ ሚና ከፍ ያለ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን እንደእናት ናትም ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.