Fana: At a Speed of Life!

ለጎርጎራ ፕሮጀክት ባለሀብቶች የፕሮጀክት መነሻ ዕቅድ እያቀረቡ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በገበታ ለሀገር የጎርጎራ ፕሮጀክት መሳተፍ የፈለጉ ባለሀብቶች ከ80 እስከ 300 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የፕሮጀክት ሐሳብ እያቀረቡ መሆኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ፡፡
እስካሁን ከ100 በላይ ባለሀብቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን የማከላዊ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ አማረ ተናግረዋል፡፡
እስከ ዛሬ ከ100 በላይ የሚሆኑ ባለሀብቶች ከ80 እስከ 300 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የፕሮጀክት ሐሳብ ይዘው ጥያቄ ማቅረባቸውንም ተናግረዋል፡፡
በጎርጎራ ሀገራዊ ፕሮጀክት የሚሳፈተፉ ባለሀብቶች የአምራች ኢንዱትሪ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ፣ የእንስስት እርባታ፣ የዓሳ ሀብት ልማት እና የግብርና ምርቶች ማቀነባበር እንደሚሠሩ ነው የተነገረው፡፡
ከአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘውን የገበታ ለሀገር የጎርጎራ ፕሮጀክት በተያዘው የጥቅምት ወር ሥራ ለማስጀመር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
ከእንጦጦ ፕሮጀክት ልምድ የወሰዱ ባለሀብቶችም ከ100 እስከ 200 የሚሆን የሰው ኃይል ወደ ሥራ ለማስገባት መነሻ እቅድ አቅርበዋል፡፡
ገበታ ለሀገር የጎርጎራ ፕሮጀክት በሃገር አቀፍ ደረጃ ሊሠሩ በእቅድ ከተያዙት ሀገር አቀፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንደኛው መሆኑን የአብመድ ዘገባ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.