Fana: At a Speed of Life!

ሉሲዎቹ የዛንዚባር አቻቸውን 5 ለ 0 አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 204 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ውድድር ዛንዚባርን የገጠመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን (ሉሲዎች) 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡

የማሸነፊያ ጎሎችን አረጋሽ ካልሳ የመሪነቱን ጎል ስታስቆጥር ሎዛ አበራ እና ቅድስት ዘለቀ ሁለት ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል፡፡

የምስራቅና የመካከለኛው የአፍሪካ የሴቶች ሴካፋ  ሻምፒዮና  ውድድር  ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን ዛንዚባርን በሰፊ ውጤት በማሸነፍ በመድረኩ ጥሩ አጀማመር ማሳየት ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.