Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት ከተፈናቃዮች ጎን ቆሞ አሰፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በደሴ ከተማ ተገኝተው በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነው።

ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተፈናቃዮቹን እየተዘዋወሩ በመጎብኘት ችግራቸውን ተመልክተው አጋርነታቸውን ገልጸዋል።

ተፈናቃዮች አሁን ያሉበት ሁኔታ የጦርነትን አስከፌነት ያሳየ ነው ብለዋል።

መንግስት ከተፈናቃዮች ጎን እንደሆነና በሚችለው ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አስታውቀዋል።

ሁሉም አካላት ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፉን እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረቡት ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ፥ የደሴ ከተማ ህዝብ ለተፈናቃይ ወገኖቹ ላሳየው ድጋፍና አጋርነት ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።

ከተለያየ አካባቢ ተፈናቅለው የመጡ ወገኖች በተቻለ መጠን በፍጥነት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መንግሥት ጥረት
እንደሚያደርግ ፕሬዚዳንቷ ጠቁመዋል።

የያዝነው አዲስ ዓመት መሰል መጥፎ ነገሮችን የማንሰማበት እንዲሆን ሁሉም ሃላፌነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

በደሴ ሆስፒታል የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎችን የተመለከቱት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፥ በሆስፒታሉ በኩል የጎደሉ ነገሮች እንዲሟሉ ይደረጋል ብለዋል።

በከድር መሐመድ እና ሃብታሙ ተ/ሥላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.