Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ የሴቶችን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስከበር በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ሴቶች ማህበር የሴቶችን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስከበር የሚያደርገውን ጥረት ማጠናከር እንደሚገባው የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ አሳሰቡ።
ማህበሩ ”ሀገር የሚሻገረው በሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ነው!“ በሚል መሪ ሀሳብ ሰባተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በባህር ዳር ከተማ አካሂዷል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ ማህበሩ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዳለበት የጠቆሙት ወይዘሮ ፋንቱ፥ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጫና ለመቀነስ የጀመረውን ትግል ማጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል።
ማህበሩ በቁርጠኝነትና በእውቀት በሚሰራ አመራር ተጠናክሮ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲሸጋገር ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡
ማህበሩ የሴት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እንዲሰራ ጠቁመው፥ ጉባኤው የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ እንዲያስቀምጥም አሳስበዋል።
የማህበሩ ምክትል ሊቀመንበር ወይዘሮ ሰላማዊት ዓለማየሁ በበኩላቸው÷ ማህበሩ ለሥርዓተ ፆታ መረጋገጥ የሚያደርገውን ትግል እንዲቀላቀሉ ለክልሉ ሴት ምሁራን ጥሪ ማስተላልፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.