Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ ለ1 ሺህ 442ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ1 ሺህ 442ኛ የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፏል፡፡

ምክር ቤቱ በአሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የመተሣሰብ እንዲሆን ተመኝቷል፡፡

የኢድ አል ፈጥር በዓል በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ መንፈሳዊ እሴቶቻቸውን የሚያዳብሩበት፣ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር ተከባብረውና ተቻችለው በጋራ የሚያከብሩት በዓል መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ፆም ወቅት ያሳየውን የመረዳዳትና የመተሳሰብ መልካም ሥራ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለቱንም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.