Fana: At a Speed of Life!

ምዕመናን የግሸን ደብረ ከርቤ አመታዊ በአልን ለማክበር ወደ ቦታው እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅድመ ዝግጅት ስራው ተጠናቆ ምዕመናን የግሸን ደብረ ከርቤ አመታዊ በአልን ለማክበር ወደ ቦታው እየገቡ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለጸ፡፡
በአሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሲደረግ የነበረው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ምዕመኑ ወደ ቦታው እየገቡ መሆኑን የመምሪያው ሀላፊ ኮማንደር እርገጤ ጌታሁን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
በአሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቂ የጸጥታ ሀይል በቦታው ተመድቧል ያሉት ሀላፊው÷ ከሰሜን ሸዋ ዞን ጀምሮ ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ተለያየን እንዲሁም ግሸን ድረስ የሚዘልቅ ኮማንድ ፖስት ተመድቦ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ብለዋል።
ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል የፓትሮል ስራ ከመስራት ባሻገር በአሉ እስከ ሚከበርበት ቦታ ድረሰ ጥብቅ የሆነ የኬላ ፍተሻ እየተደረገም ነው ተብሏል።
ስጋት ሊሆኑና ወደ ግሸን ሊያስገቡ የሚችሉ መንገዶች ዝግ መሆናቸውን የገለጹት ሀላፊው ማህበረሰቡ ጸጉረ ልውጦችን ሲመለከት ጥቆማ እየሠጠን በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል።
በተሽከርካሪና በእግረኞች ላይ የመንገድ ጥበት እንዳይፈጠር በቂ ሀይል ተመድቧል ያሉት ኮማንደሩ÷ ሰርጎ ገቦችን እና ጸጉረ ልውጦችን በህግ አግባብ እዚያው መዳኘት የሚቻልበት ጊዜያዊ ጣቢያም ተቋቋሟል ብለዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.