Fana: At a Speed of Life!

ስዊድን የኢትዮጵያን የሪፎርም ስራዎች እንደምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ሉንድኪስት ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትሯ የስዊድን መንግስት በኢትዮጵያ በትምህርት፣ ሴቶችና ህጻናት፣ ሰላም ግንባታ ዘርፎች እንዲሁም በአጠቃላይ የሪፎርም ጉዞ ላይ እያበረከተች ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የስዊድኑ አምባሳደር በበኩላቸው አገራቸው የኢትዮጵያን ሪፎርም ስራዎች አጠናክራ መደገፏን እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል መንግስት በሰሜን የሀገሪቱ አካባቢ አስፈላጊው መረጋጋት እንዲፈጠር እና በመልሶ ማቋቋም ስራ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ አንደሆነ አስረድተዋል።

በመጨረሻም ኢትዮጵያና ስዊድን ያላቸውን የሁለትዮሽ ትስስር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.