Fana: At a Speed of Life!

ሽብርተኝነትን በመከላከል የላቀ ስራ ላከናወኑ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አባላት የማዕረግ እድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኝነትን በመከላከል ረገድ የላቀ ስራ ለላከናወኑ የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት የማዕረግ እድገትና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
 
የዕውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጸጥታ አማካሪዎች፣ የልዩ ሃይል አመራርና አባላት፣ የአፍዴር ዞንና የኤሌከሪ ወረዳ አመራርና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
 
የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል መሀመድ አህመድ፥ ሽብርተኝነትን በመከላከል የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ በኤልከሪ ወረዳ ለሚገኙ ልዩ ኃይል ሠራዊት 2ኛ ብርጌድ መኮንኖች እውቅናና የማዕረግ እድገት ሰጥተዋል፡፡
 
ዕውቅና የተሰጣቸው የልዩ ሃይል አባላት የክልሉን ብሎም የአገሪቱ ሰላምና ጸጥታ የሚያናጉ አሸባሪዎች በተለይ በአልሸባብና በግብረ አበሮቹ ላይ በወሰዱት ጠንካራ እርምጃና ላሳዩት ውጤታማ የህግ ማስከበር ተልዕኮ መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራል መሀመድ ተናግረዋል።
 
ለልዩ ሃይሉ የተሰጠው ማዕረግ ከምክትል ሃምሳ አለቃ እስከ ሙሉ ኮማንደርነት መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ዕውቅናና የማዕረግ እድገት የተሰጣቸው የሰራዊት አባላት በሥራቸው ባስመዘገቡት ስኬት መሆኑን ገልፀው፥ ለአባላቱ የእንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.