Fana: At a Speed of Life!

በሀላባ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ሀላባ ዞን የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል እየተሰራ ነው።

ህብረተሰቡም የተለያዩ ባህላዊ ስልቶችን በመጠቀም መንጋውን ለመከላከል እየሰራ እንደሚገኝ ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከህብረተሰቡ አቅም በላይ በሆኑ ቦታዎች ደግሞ በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት በማድረግ የመከላከሉ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች የበረሃ አንበጣ መንጋ ተከስቶ በህብረተሰቡ እና በመንግስት ትብብር የመከላከል ስራ እየተሰራ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.