Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ውስጥ ለሚገኙ የአይ ኤስ የሽብር ቡድን ታጣቂዎች ሊቀርብ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አዲሱ ስታዲየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሀሰተኛ የዶላር ህትመት ተግባር ላይ የተሰማሩ ሁለት የካሜሮን ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ነው ግለሰቦቹ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

ተጠርጣሪዎቹ “ዶላር እናበዛለን” በማለት ከአንድ ግለሰብ 85 ሺህ የኢትዮጵያ ብር በመቀበል ያጠቆሩትን (ያባዙትን) ሃሰተኛ (ፎርጅድ) ዶላር ለግለሰቡ ለመስጠት በዝግጅት ላይ እያሉ በዛሬው እለት በፀጥታ አካላት እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

በሌላ በኩል በሀገር ውስጥ ለሚገኙ የአይ ኤስ (ISIS) የሽብር ቡድን ታጣቂዎች የጦር መሳሪያ እና ሎጂስቲክስ በማቅረብ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ባሌ ዞን ደሎመና ወረዳ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥር ከ10 በላይ የሚሆኑ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጋቸው ይታወቃል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በትናንትናው ዕለት ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በተካሄደ ዘመቻ 6 ክላሽ ከ850 መሰል ጥይት ጋር እንዲያዝ መደረጉን ኢፕድ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ይህንን የጦር መሳሪያ እና ሽብርተኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተቀናጀ ሥራ ማከናወናቸውን ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.