Fana: At a Speed of Life!

በህልውና ዘመቻው ላይ ሙያዊ አገልግሎት ለሚሰጡ 40 የጤና ባለሙያዎች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህልውና ዘመቻው ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ልዩ ኃይል ሙያዊ ድጋፍ ለሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ሽኝት አደረገ።
ከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ ሆስፒታሎች ለተውጣጡ እና ሙያዊ ድጋፍ ለሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች ለ7ኛ ጊዜ ሽኝት ማድረጉን አስታውቋል።
የጤና ባለሞያዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ እና በቢሮው ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ እንዲሁም የቢሮው ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
የጤና ባለሙያዎች በህልውና ዘመቻው ላይ ሙያዊ አገልግሎት በማድረግ የበኩላቸውን አስተፅኦ እያበረከቱ መሆኑም ተገልጿል።
የጤና ቢሮ ኃላፊዉ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በሽኝቱ ወቅት እንደገለጹት በሀገራችን የተቃጣውን የህልውና ዘመቻ ለመመከት ለተሰማራው የመከላከያ ሰራዊትና ልዩ ኃይል የጤና ባለሙያዎች በሙያቸው እያደረጉ ያለው አስተዋጽኦ በምንም ሊተካ እንደማይችል ገልጸዋል።
ኃላፊው የጤና ባለሙያዎች ሙያው የሚጠይቀውን ሁሉ አገልግሎት ለመስጠት በመወሰን ለሚያደርጉት አገልግሎት አመስግነዋል።
አክለውም ቢሮውም ሆነ ከተማ አስተዳደሩ ሁሌም ይኮራባችኃል ከጎናችሁ በመሆንም አስፈላውን ድጋፍ ያደረጋል ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.