Fana: At a Speed of Life!

በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ከ456 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

ፕሮጀክቶቹን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ መርቀዋቸዋል፡፡

ዛሬ ከተመረቁት የልማት ፕሮጀክቶች መካከል በ300 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የአርሶ አደር ገበያ ማዕከል ይገኝበታል፡፡

ከዚህ ባለፈም በ156 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የከተማ አስተዳደሩ ሕንፃም ተመርቋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በለገዳዲ ለገጣፎ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ የተገነባው 1 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ መለማመጃ መንደርም ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል አንደኛው ነው፡፡

በፕሮጀክቶቹ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በይፋ የተመረቁት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.