Fana: At a Speed of Life!

በምስል ብቻ የእፅዋትን በሽታ የሚለየው ቀመር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መቀመጫውን ጅማ ከተማ አድርጎ በሁለት ወጣቶች የተመሰረተው ደቦ ኢንጂነሪንግ ምስልን በመጠቀም ብቻ የእፅዋት በሽታዎችን የሚለይ ቀመርን አበልፅጓል፡፡
ቴክኖሎጂው በሽታውን ከለየ በኋላ መወሰድ አለባቸው የሚላቸውን እርምጃዎች ለተገልጋዮቹ የሚጠቁም ሲሆን ከአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ደንበኞች በበይነ መረብ ወይም የስልክ መተግበሪያ አማካኝነት በሚገኝ ወርሀዊ አባልነት ደንበኛ መሆን ይችላሉ ነው የተባለው፡፡
በግብርናው ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተለያዩ መፍትሄዎችን ለማፈላለግ የሚሰራው ደቦ ኢንጂነሪንግ የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ግዙፍ መረጃና ምስልን ማቀነባበር የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ስራዎቹን ያከናውናል፡፡
በተጨማሪም የተለያዩ የንግድ እርሻዎች እና የምርምር ተቋማት ስለ ስራቸው አስፈላጊውን ትንተና ለመስራት የሚያስችላቸውን የኮምፒውተር መተግበሪያ የሚያቀርብና ለሰፋፊ እርሻዎችም የድን ኪራይ አገልግሎትንም ይሰጣል ተብሏል፡፡
ባሳለፍነው ዓመት ብቻ በዋናነት በጅማና አካባቢው ለሚገኙ ከ300 በላይ ደንበኞቹም አገልግሎት ሰጥቷል፡፡
ደቦ ኢንጂነሪንግ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በተለያዩ የምህንድስና ዘርፎች በተከታተሉ ሁለት ወጣቶች አማካኝነት ምስረታውን ያገኘ ነው፡፡
የ2019 ግሪን ኢኖቬሽን እና አግሪቴክ ሰላም የቢዝነስ ውድድር እንዲሁም በሜስት አፍሪካ የኢትዮጵያ አሸናፊ መሆናቸውን ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢኒስቲቲዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.